SCORE በደቡብ ክልል ደቡብ አሞ ዞን ሁለት ወረዳዎች በአንበጣ መንጋ ለተጎዱ ሰዎችን መልሶ መቋቋሚያ የተቀናጀ ፕሮጀክት ሊተገበር ነው፡፡

ፕሮጀክቱ የሚተገበረው ከኦስትሪያ ልማት ትብበር በካሪታስ ኦስትሪያ በኩል በተገኘ /41,000,000/አርባ አንድ ሚሊዮን ብር ገደማ የገንዘብ ድጋፍ ነው፡፡ SCORE በተለያዩ ምክንያት ልማት ያልደረሰላቸው ህዝቦችን ከድህነትና ኋላቀርነት ለማላቀቅ “”የተቀናጀ ሁለንተናዊ ልማት” ዓላማ ይዞ፤ በህይወት አድን ስራ፤ በትምህርት፤ በንፁህ መጠጥ ውሃ፤ በዘላቂ የኑሮ ማሻሻያ እና በተቀናጀ ጤና ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ SCORE ላለፉት 45 ዓመታት በሚሰራባቸው አካባቢ የአካባቢው ህብረተሰብ በምግብ ራሱን ችሎና የአካባቢን ስነምህዳር በመጠበቅ ድህነትን ለመቀነስ እና ዘላቂ የሆነ ልማት ለማምጣት ከመንግስት ጎን በመሆን ብዙ ዜጎችን ተጠቃሚ በማድረግ የራሱን ድርሻ አበርክቷል፡፡ በዚህ ፕሮጀክት SCORE ደቡብ ኦሞ ዞን በሚገኙ ሁለት ወረዳዎች ማለትም በና ፀማይና ሀመር ወረዳ የሚገኙ 10 ቀበሊያት በ2012 ዓ፣ም በተከሰተው የአንበጣ መንጋ ከፉኛ የተጎዱ በመሆናቸው የተቀናጀ ድጋፍ በማድረግ ስምምነት ላይ ተደረሷል፡፡ ፕሮጀክቱ በዋናነት በጣም ለተጎዱ ግለሰቦች የጥሬ ገንዘብ ድጋፍ ማድረግን፣ የማገገሚያ ግብዓቶችን/ምርጥ ዘር ወዘተ) በማቅረብ ዘላቂነት ያለው ኑሮ ማሻሻያ መመሰረትና ወደፊት ተመሳሳይ አደጋ ቢመጣ እንዴት መመከት እንዳለባቸው አቅም ግንባታ ስራዎችን ይሰራል፡፡