April, 27, 2021 (SCORE), Bentsemay, Woyto, South Omo
Ethiopian Catholic Church social development commission, coordinating office of Sodo Sprirtan Community Outreach Ethiopia (SCORE) conducting soil and water conservation, rangeland management, and other community development works via its cash for work (CFW) programing in South Omo Zone Hamer and Bentsemay Woreda.
Bush encroachment control for better rangeland development, water conservation structures, canal, and pond clearing are chosen for the cash-for-work activities. In addition, roads that connect kebele with kebele are will be cleared. These activities will build future resilience while providing needed cash for the food purchasing power of the target community. In this cash for work activities, SCORE will reach 2700 most locust-affected households in 10 kebeles in Benatsemay and Hamer woreda
In this integrated response to people affected by locust (IRePeaL) project, SCORE will reach 4100 households in CTP (cash transfer program) in both unconditional and conditional transfer.
ሚያዚያ፤ 19፣ 2013፣ (SCORE) ፤ ወይጦ ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኢትዮጵያ
የኢትዮጲያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ማህበራዊና ልማት ኮሚሽን የሶዶ አስተባባሪ ጽህፈት ቤት ፣ ማህበረ መንፈስ ቅዱስ የማህበረሰብ አገልግሎት በኢትዮጲያ (SCORE) በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር እና ቤናትፀማይ ወረዳ ውስጥ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ፣ የግጦሽ መሬት አያያዝ እና ሌሎች የማህበረሰብ ልማት ስራዎችን በገንዘብ ለስራ (CFW) መርሃግብር በመታገዝ በማካሄድ ላይ ይገኛል ፡፡
ለተሻለ የግጦሽ ልማት ፣ አፈርና የውሃ ጥበቃ ስራዎችን ፣ ቦይ እና የኩሬ ማጽዳት እና ወረራ አረም ቁጥጥር ለገንዘብ-ለሥራ እንቅስቃሴዎች የተመረጡ ተግባራት ናቸው ፡፡ እንዲሁም ቀበሌያትን ከቀበልያት ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ይጠረጋሉ ፡፡ እነዚህ ተግባራት ሥሰሩ ለታለመው ማህበረሰብ ምግብ የመግዛት አቅም የሚያስፈልገውን ገንዘብ እየሰጡ የወደፊቱን የመቋቋም አቅም ይገነባሉ ፡፡ በዚህ የአስቸኳይ የገንዘብ ለሥራ መርሃግብር በቤናፀማይ እና በሐመር ወረዳ በሚገኙ 10 ቀበሌያት ውስጥ በጣም ብዙ የአንበጣ ተጠቂ ለሆኑ 2700 ቤተሰቦች ይደርስላቸዋል ፡፡
በዚህ ፕሮጀክት” በአንበጣ ለተጎዱ ሰዎች የተቀናጀ ምላሽ” (SCORE) ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እና ገንዘብ ለሥራ መረሃ ግብር በየገንዘብ ማስተላለፍ ፕሮግራም አማካይኝነት 4100 አባወራዎችን ይደርሳል ፡፡