31 October, 2022 (SCORE) Hamer, South Omo, Ethiopia

Ethiopian Catholic Church Social and Development Commission, Coordinating office of Soddo, Spiritan Community Outreach Ethiopia – SCORE has been implementing a project called Hamer Integrated Community Development Project in Hamer woreda four kebeles.

On October 31st, 2022 the funding agency (Horizont3000) donor representatives together with SCORE leadership paid a visit to the South Omo, Hamer Woreda to observe the current status of the project implementation!

During the visit, it was learned that the project is doing very well on its three main components, which are health, education and livelihood. As result of the activities implemented under this project, SCORE together with its partners impacted the lives of so many desperate households via women IGA (Income Generating Activity) programs, construction of new health post and rehabilitation of damaged health and veterinary posts, provision of medicines to health posts, supporting immunization, transmission of radio health programs in Hamer language through Jinka, South Omo FM, provision of motorbikes to the Woreda health center to facilitate and monitor immunization programs, provision of scholastic materials for functional adult literacy (FAL) and Early Childhood Care and Development (ECCD) students, provision of free basic computer skills training to the pastoralist students and civil servants, provision of agricultural tools for conservation agriculture participant farmers, construction of pond for animals to get water to drink and giving capacity building training for community animal health workers and health development army in different aspects are among the few ones.

 

////////////

ጥቅምት 21፣ 2015 ዓ.ም, SCORE, ደቡብ ኦሞ ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ማሕበራዊና ልማት ኮሚሽን የሶዶ ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት፣ ማህበረ መንፈስ ቅዱስ የማኅበረሰብ አገልግሎት በኢትዮጵያ – SCORE በሐመር ወረዳ አራት ቀበሌዎች የሐመር የተቀናጀ የማኅበረሰብ ልማት ፕሮጀክት የተሰኘ ፕሮጀክት ሲተገብር ቆይቷል።

ጥቅምት 21 ቀን 2022 የለጋሽ ኤጄንሲ (Horizont-3000) ተወካዮች ከ SCORE አመራር ጋር በደቡብ ኦሞ ሀመር ወረዳ የፕሮጀክቱን አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ ጎበኝቷል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ፕሮጀክቱ በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ማለትም በጤና፣ በትምህርት እና በኑሮ ማሻሻያ ዘርፍ ላይ በጥሩ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በዚህ ፕሮጀክት በተተገበሩት ተግባራት፣ SCORE ከአጋሮቹ ጋር በመሆን የብዙ ቤተሰቦችን ህይወት በሴቶች IGA (የገቢ ማስገኛ እንቅስቃሴ) ፕሮግራሞች ተጽዕኖ አሳድሯል። አዲስ የጤና ኬላ ግንባታና የተበላሹ የሰው ጤናና የእንስሳት ጤና ኬላዎችን መልሶ ማቋቋም፣ ለጤና ኬላዎች የመድኃኒት አቅርቦት፣ የክትባት ትግበራን መደገፍ፣ የሬዲዮ ጤና ፕሮግራሞች በሐመር ቋንቋ በጂንካ፣ በደቡብ ኦሞ ኤፍ ኤም እንዲተላለፍ ማድረግ፣ ለወረዳው ጤና ጣቢያ ሞተር ሳይክሎችን የክትባት ፕሮግራሞችን ለመከታተል ድጋፍ መስጠት፣ ለጎልማሳ ተማሪዎች ማንበብና መጻፍ (ፋል) እና ቅድመ ልጅነት እንክብካቤ እና ልማት (ኢሲሲዲ) ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ አቅርቦት፣ ለአርብቶ አደር ተማሪዎች እና የመንግስት ሰራተኞች ነፃ መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎት ስልጠና መስጠት፣ ለዕቀባ እርሻ ተሳታፊ አርሶ አደሮች የግብርና መሳሪያዎች አቅርቦት፣ እንስሳት የሚጠጡትን ውሃ እንዲያገኙ የኩሬ ግንባታ እና ለህብረተሰቡ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች እና የጤና ልማት ሰራዊት በተለያዩ ዘርፎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ ጥቂቶቹ ናቸው።

@Horizont3000
@AustrianDevelopmentAgency