July 31, 2021 (SCORE), Addis Ababa, Ethiopia.
Ethiopia Catholic Church Social and Development Commission – Spiritan Community Outreach Ethiopia (SCORE) program management team has concluded a one week program implementation review meeting. In this mid-year program management meeting besides the six-month program implementation review, the SCORE emergency response guideline revision task was commenced. Furthermore, a new development approach was launched. Accordingly, in addition to actively applying the existing Community-based Integrated Community Development (ICDP)approach, which SCORE has been following for more than 20 years, SCORE will pilot a School-based Inclusive Community Development (SICD)approach starting from 2022 in selected sites.
ሐምሌ 24 ቀን 2013 ዓ.ም ፣ አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ።
የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ማኅበራዊና ልማት ኮሚሽን ፣ የማህበረ መንፈስ ቅዱስ የማህበረሰብ አገልግሎት በኢትዮጵያ (SCORE)- የፕሮግራም ማኔጅመንት ቡድን የአንድ ሳምንት የፕሮግራም አፈፃፀም ግምገማ ስብሰባን አጠናቋል። በዚህ የግማሽ ዓመት የፕሮግራም ማኔጅመንት ስብሰባ ከስድስት ወር የፕሮግራም ትግበራ ግምገማ በተጨማሪ ፣ የተቋሙን የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ መመሪያ ክለሳ ተግባር አከናውኗል። በተጨማሪም የአዲስ የልማት አቀራረብ ገለፃ ተደረጎ ማስጀመሪያ ውይይት ተከናውኗል። በዚህ መሠረት ፣ተቋሙ ከ 20 ዓመታት በላይ ሲከተለው የነበረውን የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት አቀራረብን በንቃት ከመተግበሩ በተጨማሪ ፣ በ2022(እ.ኤ.አ) በተመረጡ ጣቢያዎች ውስጥ ትምህርት ቤትን መሠረት ያደረገ የማኅበረሰብ የተቀናጀ የልማት አቀራረብ ሙከራ ይጀመራል።